የቤኒሻንጉል ጉምዝ ታጣቂዎች ሰላም ለማምጣት እንደሚሠሩ ገለፁ

Your browser doesn’t support HTML5

ከቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልላዊ መንግሥት ጋራ የሰላም ሥምምነት በመፈረም ከነታጣቂዎቻቸው ወደ ክልሉ የገቡ ሸማቂ ቡድን አዛዦች ከስምምነቱ ወዲህ በክልሉ ሰላም መስፈኑን ተናግረዋል።

የቤኒሻንጉል ሕዝቦች ነጻነት ንቅናቄ /ቤህነን/ ጦር መሪ አብዱልወሃብ መሀዲ ሰላሙን ዘላቂ ለማድረግ የበኩላቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል።

የጉሙዝ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ጉህዴን/ ሊቀ-መንበር ግራኝ ጉደታ በበኩላቸው በአካባቢው አሁን ሰፍኗል ያሉትን ሰላም ለማስቀጠል እንደሚሠሩ ተናግረዋል።