መተከል ዞን ውስጥ ሰዎች መገደላቸው ተገለፀ
Your browser doesn’t support HTML5
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ድባጤ ወረዳ ዳሊቲ በምትባል ቀበሌ ውስጥ ታጣቂዎች በፈፀሙት ጥቃት የተገደሉ ቁጥራቸው የበዛ ሲቪሎች አስክሬን አለመቀበሩን እና ቁጥሩም መጨመሩን የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው የዐይን እማኞች እና ከጥቃቱ ያመለጡ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ። ከጥቃቱ ማምለጣቸውን የተናገሩ አንድ ግለሰብ ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት እስከ ዛሬ ጠዋት ድረስ ከ80 በላይ የሆኑ ሰዎች አስክሬን እንደተቆጠረ ተናግረዋል።