አዲስ አበባ —
በበጎ ፍቃደኝነት በተሰባሰቡ ኢትዮጵያውያን ዘንድሮ ለሁለተኛ ጊዜ በተካሄደው «የበጎ ሰው ሽልማት» ከልዩ ልዩ ዘርፎች የተመረጡ ሰባት ኢትዮጵያውያን አሸናፊ ሆነዋል።
በኮሚቴው ሲካሄድ የቆየው ሽልማት ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ ዕውቅና ባለው ተቋም እንደሚቀጥል አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።
የሽልማቱ ሥነ-ሥርዓት የተካሄደው ባለፈው ቅዳሜ በአዲስ አበባው ኢሊሊ ሆቴል ነበር፡፡
ሽልማቱ የተዘጋጀው በሰባት ዘርፎች ነው፡፡
በኪነ ጥበብ ዘርፍ የ91 ዓመቱ አዛውንት ተስፋዬ ሣህሉ (አባባ ተስፋዬ)፤ በባሕል፣ ቅርስና ቱሪዝም ሼኽ አብዱላሂ ሸሪፍ፤ በሰብዓዊ አገልግሎት ዘርፍ ዶ/ር በላይ አበጋዝ፤ በንግድ፣ ኢንዱስትሪ፣ ግብርናና ሥራ ፈጠራ ዘርፍ ቤተልሄም ጥላሁን፤ በማኅበራዊ አገልግሎት፣ ማኅበራዊ ሰላምና ዕርቅ ብፁዕ አቡነ ዮናስ፤ በጥናትና ምርምር ዘርፍ አምባሣደር ዘውዴ ረታ፤ እንዲሁም መንግሥታዊ ኃላፊነትን በብቃት በመወጣት አምባሣደር ቆንጂት ሥነ-ጊዮርጊስ ተሸልመዋል፡፡
ለተጨማሪ ዝርዝር ሥነ-ሥርዓቱን የተከታተለውን የእስክንድር ፍሬውን ዘገባ ያዳምጡ፡፡
Your browser doesn’t support HTML5