በኃይቅ ላይ የተከበረው ከተራና ጥምቀት በዓል

Your browser doesn’t support HTML5

በኦሮምያ ክልል ምስራቅ ሽዋ ዞን ባቱ ከተማ አቅራቢያ በሚገኘውና በጎብኚዎች ተመራጭ በሆነው የደምበል (ዝዋይ) ኃይቅ ከተራና ጥምቀት በዓል ትናንት እና ዛሬ በድምቀት ተከብሮበታል።

የባቱ ዝዋይ አመረ ብርሃን ቅዱስ ገብሬአል ገዳምና የካህናት ማሰልጠኛ መንፈሳዊ ኮሌጅ ቁጥጥር ልማት ኃላፊ መምህር ብንያም ታደለ፤ በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ ትልቅ ስፍራ በሚሰጠው ኃይቅ ላይ በዓሉ መከበሩ ሁሌም ለየት የሚያደርገው አከባበር መሆኑን ተናግረዋል። የበዓሉ ተሳታፊዎችም የበዓሉ አከባበር የበለጠ ትኩረት እንዲሰጠው ጠይቀዋል።

/ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/