ኢትዮጵያ —
ዛሬ ከባሌ ሮቤ ወደ ሻሸመኔ የሚወስደው አውራ መንገድ ዲንሾ ላይ በተቃዋሚዎች መዘጋቱ ተገለፀ።
ተቋውሞው የተቀሰቀሰው በመንግስት ፀጥታ ሀይሎች፣ ህይወቱ አልፏል የተባለውን ግለሰብ አቶ ሳዲቅ ኢብሮን የቀብር ስነስርአት ተከትሎ ነው።
በተቃውሞው ላይ ፖሊስ በተኮሰው የጭስ ቦምብ አራት ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱ የተነገረ ሲሆን የወረዳው አስተዳደር ተቃውሞውን ቀስቅሰዋል ያላቸውን ሰዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል።