የችሎት ዘገባ

Your browser doesn’t support HTML5

በአማራ ክልል ከፍተኛ የአመራር አባላት ላይ ሰኔ 15/2011 ዓ.ም. በተፈፀመው ግድያ ጉዳይ በወቅቱ የክልሉ ገዥ ፓርቲ አዴፓ ፅህፈት ቤት ኃላፊ የነበሩትና ግድያው ሲፈፀም ቦታው ላይ እንደነበሩ የተነገረው አቶ ዩሃንስ ቧያለው ዛሬ ባህር ዳር ፍርድ ቤት ቀርበው የምስክርነት ቃላቸውን ሰጥተዋል። የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በነመማር ጌትነት መዝገብ በተከሰሱ ተጠርጣሪዎች ላይ የአቃቤ ህግ ምስክሮችን መስማት ቀጥሏል።