ባሕር ዳር ላይ አድማ ተመታ

ፋይል- ባህርዳር ከተማ

በአማራ ክልል ዋና ከተማ ባሕር ዳር ከትናንት፤ ዕሁድ አንስቶ አገልግሎት ሰጭ የንግድ ድርጅቶች ሥራ ማቆማቸው ተገልጿል፡፡

በአማራ ክልል ዋና ከተማ ባሕር ዳር ከትናንት፤ ዕሁድ አንስቶ አገልግሎት ሰጭ የንግድ ድርጅቶች ሥራ ማቆማቸው ተገልጿል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ጎንደር ከተማ ውስጥ ያለው ውጥረት እንደቀጠለ መሆኑን፤ አዲስ አበባና አርባ ምንጭን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች አባላቱና ደጋፊዎቹ እየተዋከቡ መሆኑን የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት - መኢአድ አስታውቋል፡፡

አንድ ማንነታቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ የባሕር ዳር ነዋሪ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃል አድማው እስከ ነገ እንዲቀጥል የተጠራ መሆኑን አመልክተው የክልሉ መንግሥት ግን ሥራ ያቆሙ አገልግሎት ሰጭዎች ከዛሬ ከሰዓት በኋላ ጀምሮ ወደ ሥራ እንዲመለሱ አለበለዚያ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው ማሳሰቡን ገልፀዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች አባሎቻቸውና ደጋፊዎቻቸው እየተዋከቡና እየታሠሩ መሆናቸውን የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት - መኢአድ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሙሉጌታ አበበ ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል፡፡

ባሕር ዳር ላይ አገልግሎት ሰጭዎች ትናንትና ዛሬ ሥራ አቁመው መዋላቸውንና የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ግን ክፍት ሆነው አገልግሎት ሲሰጡ መዋላቸውን የተናገሩት የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ንጉሡ ጥላሁን መንግሥት ለችግሩ መፍትኄ ለመፈለግ ከሰዉ ጋር እየተነጋገረና ጥረት እያደረገ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

ባሕር ዳር ላይ አድማ ተመታ