ኢትዮጵያዊ እናት አውሮፕላን ውስጥ መንታ ህፃናት ተገላገለች

Your browser doesn’t support HTML5

ባለፈው ዓርብ የካቲት 13 ለሊት ከጅዳ ወደ አዲስ አበባ ይጓዝ በነበረ የሳውዲ ዓረብያ አውሮፕላን ተሳፍራ የነበረች አንዲት ኢትዮጵያዊት እናት ምጥ ተይዛ መንታ ሴት ህፃናትን በመውለዷ በአስመራ ዓለምቀፍ አውሮፕላን ማረፍያ እንድታርፍ ተደርጓል። አውሮፕላኑ አስመራ ዓለምቀፍ አውሮፕላን ማረፍያ ካረፈ በኋላ ኤርትራውያን ሃኪሞች ለእናትየውና መንታ ህፃናቱ አስፈላጊውን እርዳታ ተደርጎላቸዋል። በኋላም ወደ ኦሮታ ሪፈራል ሆስፒታል እንደተውሰዱና በጥሩ ሁኔታ ላይ እንዳሉ ታውቋል።