“የልብ ትርታ መረበሽ ብዙውን ጊዜ ያንን ያህል ለጤና የሚያሰጋ ነገር የለውም። ምን ሊሆን ይችላል በሚል ግለሰቡን ማሳሰቡ ነው። ነገር ግን ረዘም ላለ ጊዜ ተደጋግሞ ሲመጣ፥ ከእርሱ ጋር ተያይዞም የትንፋሽ ማጠር እና ደረት ላይ ጫና በሚሰማበት ጊዜ ግን ሌላ ክትትል ሊያስፈልገው ይችላል።” ዶ/ር ውብሸት አየነው የልብ ሕክምና ከፍተኛ አማካሪ ሃኪም ናቸው።
Your browser doesn’t support HTML5
“ፈጣንና የበዛ” ልበ ትርታ ምንነት፥ ምልክቶቹ፥ የጤና እክል ሆኖ የሚወሰድባቸው ሁኔታና ሕክምና፤ “ሃኪምዎን ይጠይቁ” በተከታታይ የሚመለከታቸው ጥያቄዎች ናቸው።
የልብ ትርታ መረበሽ ከድንገተኛ የሥሜት መታወክ ባሻገር መቼ ይሆን አሳሳቢና ክትትል የሚሻ የጤና ሁከት የሚሆነው? ለሕክምና ወደ ሃኪምዎ ሲሄዱስ እንዴት ይሆን መዘጋጀት የሚኖርብዎ?
ዶ/ር ውብሸት አየነው፤ ሞያዊ ማብራሪያውን የሚሰጡን በዚህ በዩናይትድ ስቴትስ የሜነሶታ ክፍለ ግዛት የHennepin County የሕክምና ክሊኒክ የልብና የውስጥ ደዌ ከፍተኛ አማካሪ ሃኪም ናቸው። ለጥያቄዎቻችን ሞያዊ ማብራሪያ ይሰጣሉ።