የማኅበራዊ ግንኙነት አዋኪነት ዝንባሌ የአዕምሮ ሕመም ወይስ እኩይ ጠባይ?

anti-social personality disorder

anti-social personality disorder

ለሌሎች ክብር ማጣት፤ ትክክለኛውን ከስሕተቱ ያለመለየት ያለመቻል። ምክኒያት የለሽ በሆነ የበረታ ጥላቻና ክፋት መጠመድና ንጹሃንን የመበደል ፍላጎት ከዋነኞቹ ምልክቶች ውስጥ ናቸው። ሁሉን አዋቂ ነኝ ባይነትና አንዳንዴም እውነተኛ ጠባይን በመሸሸግ መልካም የሚመስል ጠባይ በማሳየት ሌሎች በማደናገር ለግል ጥቅም አመቺ ሁኔታ ለመፍጠር ማውጠንጠን ይገኙበታል።

ይህ ታዲያ እኩይ ጠባይ ብቻ አይደለም። የአእምሮ ሕመም ጭምር እንጂ። በሕምናው ቋንቋ በእንግሊዝኛ antisocial personality disorder በመባል ይታወቃል።

ለመሆኑ የዚህ ሕመም ምንጩ ምን ይሆን? በሕክምና ይረዳል? ሥር ከመስደዱ አስቀድሞስ መከላከል ይቻል ይሆን?

በተከታታይ የሚቀርበው የሃኪምዎን ይጠይቁ ቅንብር የህመሙን ምንነት፥ ዓይነተኛ መለያዎች፥ የሕክምና አማራጮች ጨምሮ ይዳስሳል።

ሞያዊ ትንታኔውን የሚሰጡን ፕሮፌሰር ዮናስ እንዳለ ገዳ፥ በሜዮ ክሊኒክ፥ የነርቭና የአዕምሮ ሃኪም ናቸው።

Your browser doesn’t support HTML5

የማኅበራዊ ግንኙነት አዋኪነት ዝንባሌ እና የአዕምሮ ሕመም .. የመጀመሪያውን ክፍል ከዚህ ያድምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

ሁለተኛውን ክፍል ከዚህ ያድምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

የማኅበራዊ ግንኙነት አዋኪነት ዝንባሌ እና የአዕምሮ ሕመም .. የመጨረሻውን ክፍል ከዚህ ያድምጡ።