ቅርሶች እየተመለሱ መሆኑን ቅርስ አስመለሽ ኮሚቴው አስታወቀ

Your browser doesn’t support HTML5

ከኢትዮጵያ በተለያዩ መንገዶች ወጥተው አውሮፓና አሜሪካ ውስጥ የነበሩ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ እየተመለሱ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቅርስ አስመለሽ ኮሚቴ አስታወቀ፡፡ ከተሠሩ 500 ዓመታት የሚያልፋቸውን የእጅ ጥበብ ጨምሮ ከ20 በላይ ታሪካዊና መንፈሳዊ ቅርሶች በሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ መመለሳቸውን የኮሚቴው ሰብሳቢ ዶክተር አባተ ጌታሁን ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።