የሰሜን አፍሪቃዊቱን አገር ግብፅን ሰቅዞ የሰነበተው ሠሞንኛ የፖለቲካ ቀውስ ዛሬም ቀጥሎ ውሏል።

Supporters of President Hosni Mubarak fight with anti-Mubarak protesters in Cairo

ሙባረክ በስልጣን እስከ ቆዩ ድረስ ተቃዋሚው ወገን ዋስትና የለውም። የሚቀጥለው ምርጫ ከቀደሙት ለየት ያለ፥ ነፃና ገለልተኛ ምርጫ ይሆናል፤ የሚል እምነት የላተውም። ስለዚህ አስተማማኝ ለውጥ ይመጣል ብሎ ማመን ስለሚከብድ ነው፤ ፕሬዝዳንት ኦባማ፥ ሙባራክ አሁኑኑ ለውጥ እንዲያመጡ ጫና በማድረጉ የገፉበት።

ተጥሎ የቆየው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቢነሳና መንግስቱ በወሰደው ዕርምጃ ተቋርጦ የነበረው የኢንተርኔት አገልግሎት የተመለሰ ቢሆንም፤ በሰላማዊነቱ የተወደሰው ኅዝባዊ እንቅስቃሴ ግን አንዳንዶች «መንግስቱ ያደራጀው፤» ባሉት እንቅስቃሴ፥ የሙባረክን ከስልጣን መውረድ ከሚጠይቁ ሠልፈኞች ጋር መጋጨቱ ተዘግቧል።

የግብፅን ውሎና አዳር፥ የኅዝባዊ አመፁን ቀጣይ የሂደት አቅጣጫና የዩናይትድ ስቴትስና የሌሎች ምዕራብ አገሮች ሚና በቀጣዩ ተከታታይ ሁለት ክፍል ውይይቶች እንገመግማለን።
ትንታኔውን የሚሰጡን የፖለቲካ ሳይንስ አጥኚው አቶ ጃዋር መሃመድ ናቸው።

ክፍል ኣንድ

ክፍል ሁለት