የአውሮፓ የመገናኛ ብዙሃን የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በጠና መታመማቸውን በትናንትናው ዕለት የዘገቡትን አቶ በረከት አስተባብለዋል።
ኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ዛሬ ከሰዓት በኋላ የማስተባበያ የጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሃኪሞች የህክምና እረፍት እንዲወስዱ ተመክረው፤ በእረፍት ላይ መሆናቸውንና ከህመማቸው ሲያገግሙ በቅርቡ ወደስራቸው እንደሚመለሱ የኢትዮጵያ የኮሚውኒኬሽንስ ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ በረከት ስምዖን ለጋዜጠኞች ገልጸዋል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ የጤና ሁኔታ “ከስራ ብዛት የመነጨና ለክፉ የማሰጥ ነው፣” ብለዋል አቶ በረከት።
ዛሬ ከሰዓት በኋላ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የጤና ሁኔታ፣ በሙስሊሞች የተቃውሞ ሰልፎችና በቅርቡ ከባድ የእስር ቅጣት በተጣለባቸው ጋዜጠኞችና የፖለቲካ ተቃዋሚዎች ዙሪያ ያተኮረ ነበር።