ሱዳን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ካርቱም የላካቸው የጦር መሳሪያዎች ሕጋዊ ናቸው አለች

Your browser doesn’t support HTML5

ሱዳን የዜና ወኪል የሆነው ሱና የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ ቅዳሜ ዕለት ወደ ካርቱም ያጓጓዛቸው የጦር መሳሪያዎች በሱዳን መንግስት መወረሳቸው መዘገቡን ተክትሎ የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ ወደ ሱዳን ካርቱም ያጓጓዝኳቸው የጦር መሳሪያዎች ሕጋዊ ሰነድ ያላቸው እና በሱዳን መንግስት የሚታወቁ ናቸው ሲል ለአሜሪካ ድምጽ ምላሽ ዛሬ ጠዋት ምላሽ ሰጥቷል፡፡ በሌላ በኩል አሁን ማምሻውን የሱዳን የሃገር ውስጥ ሚኒስቴር ለሮይተርስ በሰጠው መረጃ የጦር መሳሪያዎቹን ሕጋዊነት አረጋግጧል