ማርቲን ሉተር ኪንግ

Your browser doesn’t support HTML5

እአአ ሚያዝያ 1968 አንድ ጠመንጃ አንጋች፣ ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየርን በጥይት ገደለ። በዚያም የሲቪል መብቶች እንቅስቃሴ መሪውን አጣ። ኪንግ የተገደሉበትን ቀን ተከትለው ባሉ ቀናት፣ በመቶዎች በሚቆጠሩ የአሜሪካ ከተሞች፣ የተቃውሞ ሰልፎችና ሕዝባዊ አመፅ ተቀጣጠለ። በዚያ ሳቢያ ክፉኛ የተጎዳችው የሀገሪቱ ዋና ከተማ ዋሺንግተን ዲሲ ስትሆን፣ ዛሬ ከ50 ዓመታት በኋላ ብዙ ለውጦች የተካሄዱባት መሆኗን እንገነዘባለን።