በኢትዮጵያ ፕሬስ ይዞታ ላይ የተካሄደ ውይይት

Your browser doesn’t support HTML5

የኢትዮጵያን የመገናኛ ብዙሃን ምህዳር የማሻሻሉና የማስፋቱ ሂደት ከሀገሪቱ ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ ጋር በተያያዘ መቀዛቀዙን የዘርፉ ባለሞያዎች ተናግረዋል።

ባለፈው ዓመት በፓርላማ የፀደቀው የመገናኛ ብዙሃን ሕግ ከፍተኛ እመርታ ያሳየ መሆኑን የገለፁት ባለሞያዎቹ ለተግባራዊነቱ መስራትና ቀደም ሲል የነበረውን መነቃቃት ማስቀጠል እንደሚገባም ዛሬ በባህር ዳር ከተማ በተካሄደው የውይይት መድረክ ላይ አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ ሚድያ ማሻሽያ ለውጦች፣ ተግዳሮቶች እና ቀጣይነት ላይ የሚመክር ውይይት የዘርፉ ባለሞያዎች እና ምሑራን በተገኙበት በባህር ዳር ከተማ ተካሂዷል።

የአስቴር ምስጋናው ዘገባን ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ።