ግብርና በቀውስ ወቅት የተለያዩ ተፅዕኖዎች እንደሚደርስበት ተነገረ

Your browser doesn’t support HTML5

በኢትዮጵያ ልዩ ልዩ አካባቢዎች ያጋጠመው ጦርነት፣ ጥቃት፣ ግጭት እና ድርቅ፣ እንዲሁም እነዚኽ አደጋዎች የሚያስከትሉት መፈናቀል፣ ወቅታዊ በኾነው የግብርና ሥራ ላይ ከፍተኛ ጫና እንደሚፈጥር ባለሞያዎች ይናገራሉ፡፡

በዓለም ላይ እየታየ የሚገኘው የማዳበሪያ ዋጋ መናርም፣ ከግብርና ሥራዎች አንዱ በኾነው የእርሻ እንቅስቃሴ ላይ ተጽእኖውን በማሳረፍ ላይ እንዳለ ይገልጻሉ፡፡

አርሶ አደሮች፣ የእርሻ ግብአቶችን በተፈለገው መጠንና በወቅቱ ካላገኙ መፍትሔው ምን ሊኾን እንደሚችል ባለሞያዎቹ ምክር እየሰጡ ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት በበኩሉ፣ በሰው ሠራሽ እና ተፈጥሯዊ ምክንያቶች፣ በእርሻ ሥራ ላይ የሚደርሰውን የመስተጓጎል ተጽዕኖ ለማቃለል፣ የቀውስ ምላሽ ምክረ ዐሳቦችን በመስጠት ላይ እንደኾነ አስታውቋል፡፡

/ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/