የሱዳን ተፋላሚ ወታደራዊ ኃይሎች ግጭት ቀጣናዊ ተጽእኖ

Your browser doesn’t support HTML5

በአፍሪካ ሦስተኛ ግዙፍ ሀገር የኾነችው ሱዳን የገባችበት ውጥረት፣ የአገሪቱን ግዛት ተሻግሮ ለምሥራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ የሚተርፍ መዘዝ ሊኖረው እንደሚችል የተጽእኖ ተንታኞች እየተናገሩ ይገኛሉ። ከእነዚህ ምሁራን መካከል፣ አህጉሩን በሚመለከቱ ሕግ እና ፖለቲካ ተኮር ጉዳዮች የሚታወቁት ዶር. አደም ሑሴን አንዱ ናቸው። በኔዘርላንድስ የሚገኘው፣ ዓለም አቀፍ የዴሞክራሲ እና የምርጫ ድጋፍ ኢንስቲትዩት ባልደረባ የኾኑት ዶር. አደም ሑሴን፣ ስለ ሱዳን ውስጥ ግጭት እና ተያያዥ ጉዳዮች ሐሳባቸውን አጋርተውናል።

ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።