በኬንያ ምርጫ አንድ አዲስ እጩ መጥተዋል

Your browser doesn’t support HTML5

በኬንያ አንድ አዲስ እጩ ተቀባይነትን እያገኙ በመምጣታቸው የፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤትን ሊቀይረው ይችላል ተባለ።

በኬንያ የሚካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ጥቂት ሳምንታት በቀረበት በዚህ ወቅት፣ አንድ አዲስ እጩ ታዋቂነትን እያገኙ መምጣታቸው የምርጫውን የመጨረሻ ውጤት ባልተገመተ ሁኔታ ሊደመድም እንደሚችል ተንታኞች እየተናገሩ ነው።

ጆርጅ ዋጃኮያ የተባሉት እኚህ እጩ፣ ከፊት እየመሩ ካሉት ሌሎች ዕጩዎች፣ ራይላ ኦዲንጋ እና ዊሊያም ሩቶ፣ ራቅ ብለው በመከተል ላይ ቢሆኑም፣ የአስተያየት መስጫ ውጤቶች እንደሚያሳያዩት ተወዳዳሪው ሃሺሽን ሕጋዊ አደርጋለሁ ብለው መንቀስቀሳቸው ብዙ ደጋፊ እንዲያስከትሉ እያደረጋቸው ነው።