አምነስቲ ኢንተርናሽናል ስለታሰሩ ሰዎች
Your browser doesn’t support HTML5
የሠብዓዊ መብት ተሟጋቹ አምነስቲ ኢንተርናሽናል የኦሮምያ ፖሊስ የክልሉ ፍርድ ቤት በነፃ እንዲለቀቁ ያዘዛቸውን ሶስት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኃላፊዎችንና ሁለት የኦሮምያ ኒውስ ኔትዎርክ ጋዜጠኞችን እንዲለቅ ጠየቀ። በአምነስቲ ኢንተርናሽናል ምሥራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ቢሮ የኢትዮጵያ ጉዳዮች ሰብዓዊ መብት አያያዝ አጥኚ አቶ ፍሰሃ ተክሌ ግለሰቦቹ በፖሊስ አለ አግባብ ታስረዋል ብለዋል። የኦሮምያ ፖሊስ ኮሚሽነር ታስረዋል ስለተባሉ ሰዎች መረጃ የለኝም ይላሉ።