የአካል ጉዳተኞች ውዝዋዜ ሥልጠና ጀማሪው ኢትዮጵያዊ

Your browser doesn’t support HTML5

የኢትዮጵያ ዘመናዊ እና ባህላዊ ውዝዋዜ አሰልጣኝ ታደሰ ገብሬ ወይም በመድረክ ስሙ “ጃክሰን” ለአስራ አምስት ዓመታት አካል ጉዳተኞችን በውዝዋዜ ጥበብ ሲያሰለጥን ቆይቷል።

ጃክሰን ከሁለት ዓመት በፊት በፊት ባጋጠመው የጀርባ ጉዳት ምክኒያት ከመድረክ ርቋል። ከስድስት ወራት በፊት ጀርባው ላይ ቀዶ ሕክምና እንደተደረገለት ገልጾ “ሥራ ስለማልሠራ አሁን ትንሽ ኑሮ ከብዶኛል” ብሎናል።

/በጃክሰን ሕይወት ዙሪያ በጋቢና ቪኦኤ የተሰናዳውን ዘገባ ከተያያዘው ፋልይ ይከታተሉ/