ጄነራል ተፈራ ማሞ ባህርዳር በእስር ላይ በቆዩበት ለተጨነቁላቸው ምስጋና አቅርበዋል

Your browser doesn’t support HTML5

ባላለፉት 25 ቀናት በእስር ላይ የቆዩት የአማራ ክልል ልዩ ኃይል አዛዥ ብሪጋዲየር ጄነራል ተፈራ ማሞ መኖሪያ ቤታቸው እንደገቡ ከአሜሪካ ድምፅ ጋር አጭር የስልክ ቃለምልልስ አድርገዋል።

"ለተጨነቁልኝ" በማለት ከጎናቸው ለነበሩ በሙሉ ምስጋና ያቀረቡት የቀድሞው የአማራ ክልል ልዪ ኃይል አዛዥ ብርጋዲየር ጀነራል ተፈራ ማሞ በተያዙበት ሰዓት ከነበረው ሁኔታ ውጭ በእስር ቤት የደረሰባቸው የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንደሌለ ተናግረዋል።

ከትናንትና ጀምሮ የዋስትና ክርክሩን ያዳመጠው በባሕርዳር ከተማ ያስቻለው የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጀነራሉ በ30 ሺ ብር ዋስ እንዲፈቱ መወሰኑን ጠበቃቸው አብራርተዋል።

ዘገባው የአስቴር ምስጋናው ነው።