በአማራ ክልል ቀዝቅዞ የነበረው ቱሪዝም እየተነቃቃ ነው
Your browser doesn’t support HTML5
ለፉት ሦስት ዓመታት የቱሪዝም ዘርፉ በመቀዛቀዙ ምክንያት ከሥራ ወጥተው የነበሩ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ወደ ሥራ መመለሳቸውን የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታውቋል።
ለዘርፉ መቀዛቀዝ ዋና ምክንያት ኮቪድ 19ና ጦርነቱ መሆናቸውን የጠቆሙት የቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ኤርሚያስ መኮንን በዓለም ዙሪያ ያለው ትውልደ ኢትዮጵያ ወደ ትውልድ ሀገሩ መግባቱን ተከትሎ የቱሪዝም እንቅስቃሴ መነቃቃቱን ተናግረዋል።