በአማራ ክልል ውስጥ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ መስራትን አስመልክቶ አስተያየት
Your browser doesn’t support HTML5
በቅርቡ በአማራ ክልል ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸው ስምምነት ላይ መድረሳቸውን መገናኛ ብዙኃን ዘግበውታል፡፡ በስምምነቱ ዙሪያ የወሎና ባህርዳር ዩኒቨርሲቲዎች ምሁራን ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ በተናጠላዊ እንቅስቃሴ የህዝብን ችግር መፍታት፣ የህዝብን ጥያቄ መመለስ አይቻልም የሚሉት ምሁራኑ ስምምነቱ ወደ አዲስ ምእራፍ የሚያሸጋግር መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡