ከኦሮምያ ክልል የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር አንድ ሚልየን መጠጋቱን አማራ ክልል አስታወቀ

Your browser doesn’t support HTML5

ከኦሮምያ ክልል አራቱም ዞኖች ተፈናቅለው አማራ ክልል የገቡ ተፈናቃዮች ቁጥር አንድ ሚልየን መጠጋቱን የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን አስታወቀ።

የኮሚሽኑ የቅድሚያ ማስጠንቀቂያና ምላሽ ዳይሬክተር ጌቴ ምህረቱ ካለፈው ጥቅምት ወር ጀምሮ በድጋሚ በተቀሰቀሰው ግጭት ከአራቱም የኦሮምያ ክልል ዞኖች ተፈናቅለው አማራ ክልል የሚገቡ ተፈናቃዮች ቁጥር በየዕለቱ መጨመሩን ተናግረዋል። ትናንት ሰኞ ጥር 15/2105 800 ተፈናቃይ ባህር ዳር መግባቱን ገልፀዋል።

የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ተፈናቃዮች ከሁለት እስከ አራት ሳምንት የፈጀ የእግር ጉዞ አድርገው ባህር ዳር መድረሳቸውን ተናግረዋል።

በኦሮምያ ክልል በቀጠለው የጸጥታ ችግር ምክንያት ንጹሃን ዜጎች በክልሉ ውስጥና ከክልሉ ውጭ ወደ አማራ ክልል እየተፈናቀሉ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ /ኦቻ/ ሰሞኑን ባወጣው ሪፖርት ጠቁሟል።