ዳባት የተጠለሉ ተፈናቃዮች የገጠማቸው ፈተና

Your browser doesn’t support HTML5

ከሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ጋር በተያያዘ ከትግራይ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ወረዳ “ሽመላኮ” በተባለው መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ተፈናቃዮች ከፍተኛ የምግብ እጥረት እንዳጋጠማቸው ተናግረዋል ።

ተፈናቃዮቹ እንደሚሉት ከጥቅምት መጨረሻ ወዲህ ምንም አይነት የምግብና ንፅህና መጠበቂያ ባለማግኘታቸው ህፃናት ልጆቻቸው ለበሽታ እየተጋለጡ ነው።

የሰሜን ጎንደር ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ፅ/ቤት በበኩሉ ችግሩ መኖሩን አምኖ በመጠለያ ጣቢያ ከሚገኙት በተጨማሪ ከማኅበረሰቡ ጋር ተቀላቅለው የሚኖሩ 41ሺ የሚሆኑ ተፈናቃዮች እርዳታ እያገኙ እንዳልሆነ አመልክቷል ።

የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን በበኩሉ ከፌዴራል አደጋ ሥጋት አና ሥራ አመራር ኮሚሽን ጋር እየተነጋገርኩ ነው ብሏል።