በውጫሌ ከተማ በወጣቶችና በፀጥታ ኃይል መካከል ግጭት ተፈጠረ

Your browser doesn’t support HTML5

በደቡብ ወሎ ዞን አምባሰል ወረዳ ውጫሌ ከተማ አካባቢ ለመንግሥት ሰራተኞች የቤት መስሪያ የተሰጠው ቦታ “ለእኛ ይገባል” በሚሉ ወጣቶችና በፀጥታ ኃይሉ መካከል በተፈጠረ ግጭት የሞትና የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡ የሞቱትንና የቆሰሉትን ሰዎች ቁጥር ከገለልተኛ ወገን ለማጣራት ጥረት እየተደረገ ነው፡፡