ወልቂጤ አድማ ላይ ናት

Your browser doesn’t support HTML5

በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ባለፈው ሳምንት በመጠጥ ውሃ ችግር ምክኒያት ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ የወጡ ሦስት ሰዎች መገደላቸውን ተከትሎ የተደረገው ከቤት ውስጥ ያለመውጣት አድማ ዛሬም ቀጥሏል። ባንክ ቤቶችን ጨምሮ የመንግሥት እና የግል ተቋማት ዝግ መሆናቸውን ነዋሪዎቹ ገልጸዋል።

አድማውን ያደረጉት ሰላማዊ ሰዎችን ገድለዋል የተባሉ የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ለሕግ እንዲቀርቡና ለሟች ቤተሰቦች ካሳ እንዲከፈል ለማድረግ መሆኑን ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።

ከተማው ወደ መደበኛ እንቅስቃሴ እንዲገባ ጥረት እያደረገ መሆኑን የገለፀው የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አመፅ አስነስተዋል የተባሉ 15 ሰዎችን ማሰሩን ገልጿል።

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።