ወልቂጤ አራት ሰዎች በፀጥታ ኃይሎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለፁ

Your browser doesn’t support HTML5

- ፖሊስ የሞቱት ሰዎች ሦስት ናቸው ብሏል

በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ከክልሉ የፀጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት አራት ሰዎች መገደላቸውንና 17 መቁሰላቸውን ነዋሪዎች ገለፁ። በአካባቢው ለአንድ ዓመት ያህል የመጠጥ ውሃ በመቋረጡ አቤቱታ ለማሰማት አደባባይ መውጣታቸውን አስተያየታቸውን ለአሜሪካ ድምፅ የሰጡ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

የወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ስፔሻላይዝድ ሪፌራል ሆስፒታል ቆስለው ወደ ሆስፒታሉ ከመጡ 16 ሰዎች ውስጥ ሁለቱ ወዲያውኑ ሲሞቱ ሁለቱ ከፍ ላለ ሕክምና ወደ አዲስ አበባ መላካቸውን ገልጿል።

የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በከተማው በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ሁከት መፈጠሩን ገልፀው የሞቱት ሰዎች ሦስት መሆናቸውና ስምንት መቁሰላቸውን አስታውቋል።