የልጆች የማኅበራዊ ብዙኃን መገናኛ አጠቃቀም ግራ እና ቀኝ

Your browser doesn’t support HTML5

ሕፃናት እና አዳጊዎች፣ ማኅበራዊ ብዙኃን መገናኛን መጠቀማቸው፣ አዎንታዊም አሉታዊም ተጽእኖ እንዳለው የመስኩ ተመራማሪዎች ያስገነዝባሉ፡፡ ይህም ኾኖ፣ በዩናይትድ ስቴትስ፣ የልጆችን የማኅበራዊ ትይይዝ መድረኮች አጠቃቀም፣ በሕግ ለመግራት እየተደረገ ያለው ግፊት እየበረታ መጥቷል፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ዘጋቢዋ ቬሮኒካ ባልዴራስ ኤግሊስያስ ያናገረቻቸው ተመራማሪዎች፣ በአማራጭ መድረኮች የተሞሉትን ማኅበራዊ የመገናኛ አውታሮች መጠቀም፣ በሕፃናት እና በአዳጊዎች ላይ፣ በአዎንታም ኾነ በአሉታ የሚያስከትለውን ተጽእኖ(ግራ እና ቀኝ) ለይተው ያስረዳሉ፡፡