“የሽብር ጥቃት አደጋ ከአልቃይዳው መሪ ጋር አብሮ አልተቀበረም” - ዩናይትድ ስቴትስ

Your browser doesn’t support HTML5

ዩናይትድ ስቴትስ በቅርቡ አፍጋኒስታን ውስጥ የአልቃይዳውን መሪ በመግደል በሽብር ቡድኑ መሪው ላይ የወሰደችው እርምጃ ለሽብር ቡድኑ ታላቅ ሽንፈት ነው።

እርምጃው በመካከለኛው ምስራቅ፣ አፍሪካ እና እስያ ውስጥ ባለው የሽብር እንቅስቃሴ ላይ ምን ዓይነት ተጽዕኖ ያሳድር ይሆን?

እርምጃውን ተከትሎ ዋይት ኃውስ በሰጠው መግለጫ ላይም “ይህ በመሳካቱ ከሌሎች ማናቸውም ሽብር ስጋቶች ላይ ዓይናችንን አናነሳም፣ አንዘናጋም” ሲል፤ ዓለም አቀፍ ሽብርተኝነትን የሚያጠኑ ተንታኞች በበኩላቸው ዩናይትድ ስቴትስ ንቃት ያልተለየው ክትትል ማድረግ እና በትዕግስት መጠበቋን መቀጠል አለባት ይላሉ።