የዓድዋ ድል በዓል መከበር የሰላም ተስፋን እንደሚያጠናክር ነዋሪዎች ገለጹ

Your browser doesn’t support HTML5

በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የዓድዋ ድል በዓል አከባበር፣ ከሦስት ዓመት መስተጓጎል በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በዛሬው ዕለት በታሪካዊቷ ዓድዋ ተከብሯል።

የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው የከተማው ነዋሪዎች፣ "በዓሉ በመከበሩ ለሰላም ያለን ተስፋ እንዲጨምር አድርጓል፤" ብለዋል።

በሌላ በኩል፣ ከአሁን በፊት በእግር ወደ ዓድዋ ጉዞ ያደርጉ የነበሩ ወጣቶች፣ ዘንድሮ ያለመሳተፋቸውን የገለጹት አቶ ካሌብ፤ “ወጣቶቹ ቢሳተፉ፣ የበዓሉ ድምቀት ይበልጥ ይጎላል፤” ብለው እንደሚያምኑ አመልክተው፤ በሚቀጥለው ዓመት ግን ይሳተፋሉ የሚል ተስፋ እንዳላቸው ጠቁመዋል።

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡