ደቡብ አፍሪካን የኃይል መቆራረጥ እየጎዳት ነው

Your browser doesn’t support HTML5

ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ የተቃዋሚው ዴሞክራቲክ ህብረት ፓርቲ አባላት ደጋፊዎች የሃገሪቱን ምጣኔሃብት እያሽመደመደ የሚገኘውን የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ተቃውመው ዛሬ አደባባይ ውለዋል።

እስከዛሬዎቹ ከፍተኛ የሆነው ይህ የኃይል መቆጠራረጥ አነስተኛ ንግዶችን ውድ ለሆኑ ጀኔሬተሮች ሲዳርጋቸው ህልውናቸው ላይ ሥጋት መደቀኑን ይናገራሉ።

ከእነዚያ ቢዝነሶች መካከል መንግሥት ለኮቪድ 19 በሰጠው ድጋፍ በሩን ለአገልግሎት ክፍት በማድረጉ በሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፖሳ የተሞገሰው የሶዌቶ ክሬመሪ የሚገኝበት ሲሆን ክሬመሪና ሌሎች በርካታ ቢዝነሶች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተከታተለ የሚደርሰውን የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ መቋቋም አዳጋች ሊሆንባቸው እንደሚችል ተነግሯል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ዘገባ ይመልከቱ።