አቡነ ፍራንሲስ በደቡብ ሱዳን ሰላም እንዲሰፍ ተማፀኑ

Your browser doesn’t support HTML5

የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አቡነ ፍራንሲስ በደቡብ ሱዳን ያደረጉትን የሦስት ቀናት ጉብኝት አጠናቅቀው ከትናንት በስቲያ እሁድ ወደ ሮማ ተመልሰዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ጉብኝታቸውን ከማጠናቀቃቸው በፊት በጁባ የጆን ጋራንግ መካነ መቃብር አንድ መቶ ሺህ የሚሆኑ ምዕመናን በተገኙበት ሥርዓተ ጸሎት ላይ በሀገሪቱ ሰላም እንዲሰፍን አጥብቀው ተማጽነዋል።