በሰው አምሳል ከዕንጨት የተጠረቡ ግዙፍ ቅርጾች - የሰሜናዊ ምዕራብ ፓስፊክ ሞገሶች

Your browser doesn’t support HTML5

በሰው ቁመና አምሳል ከዕንጨት ተጠርበው የተሠሩት ስድስት ግዙፍ የዕንጨት ቅርጾች፣ ሰሜናዊ ምዕራብ ፓሲፊክ እየተባለ የሚታወቀው የሰሜናዊ ምዕራብ ዩናይትድ ስቴትስ ሞገስ ኾነዋል፡፡

በቅርጾቹ ቀልባቸው የተሳቡ ሰዎች፣ ጫካው ውስጥ በፍለጋ እንዲያገኟቸው በማነሣሣት፣ የተለየ አዝናኝ ስሜት እየፈጠሩ ይገኛሉ። ከአካባቢው ነባር ጎሣዎች ተወላጆች ጋራ በመተባበር፣ ይህን ቀልብ ሳቢ ፕሮጀክት የፈጠረው፣ የተፈጥሮ አካባቢ ጥበቃ ተሟጋቹ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍ ያለ ዕውቅና ያገኘው የቅርጻቅርጽ ባለሞያው ቶማስ ዳምቦ ነው።

ናታሻ ሞዝጎቫያ ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።