የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የትግራይን ሕዝብ ይቅርታ ጠየቀች

Your browser doesn’t support HTML5

ቤተ ክርስቲያኒቱ፣ ሐዋርያዊት እና ታሪካዊት እንደሆነች የጠቀሰው ቅዱስ ሲኖዶስ፣ የአገርን ሰላም እና የሕዝብን አንድነት ለመጠበቅ ባላት ተቋማዊ ሚና፣ መነሻውን በትግራይ ክልል ያደረገው የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት በወቅቱ እንዲቆም መግለጫ ባለማውጣቷ፣ በጦርነቱ ሒደት እና ፍጻሜ፣ በቦታው ተገኝታ ባለማጽናናቷ እና የተወሰነውን ሰብአዊ ድጋፍ በጊዜው ማድረስ ባለመቻሏ፣ ለተፈጠረው ቅሬታ እና አለመግባባት፣ ቅዱስ ሲኖዶስ በይፋ ይቅርታ ጠይቋል፡፡

በጉዳዩ ላይ አስተያየት የጠየቅናቸው፣ የሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ሀገረ ስብከት ሽረ እንዳሥላሴ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ፣ ይቅርታው ከመሸ በኋላ ለይምሰል የተጠየቀ በመሆኑ፣ ተቀባይነት የለውም፤ በጀመርነው እንቀጥላለን፤ ብለዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።