በኦሮምያ እና ሶማሌ ክልሎች ኮሌራ እየተስፋፋ ነው

Your browser doesn’t support HTML5

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ /ኦቻ/ በኦሮምያ እና በሶማሌ ክልል የኮሌራ ወረርሽን እየተስፋፋ መሆኑኑ አስታወቀ።

በባሌ፣ ጉጂና ሶማሌ ክልል ሊበን ወረዳ ተከስቶ የነበረው በሽታ ወደ ምዕራብ አርሲ ዞን ተዛምቶ እስካሁን 28 ሰዎች መሞታቸውን ድርጅቱ አስታውቋል።