በኦሮምያ ክልል የወባ በሽታ ሥርጭት እያሻቀበ ነው

Your browser doesn’t support HTML5

በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ሃያ በመቶ መጨመሩን የገለጸው ቢሮው ባለፈው ዓመት በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር 157 ሺህ ገዳማ ሲሆን ዘንድሮ ደግሞ ከ251 ሺህ በላይ ሰዎች ለበሽታው መጋለጣቸውን የጤና ቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ አበራ ጉዲሳ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል።

በክልሉ አራት ከተሞች፣ አስራ ሶስት ዞኖች እና 65 ወረዳዎች ውስጥ የበሽታው ሥርጭት እንደሚገኝ ቢሮው ገልጿል።

የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ነዋሪዎችም በከተማቸው በሽታው መስፋፋቱን ይገልፃሉ።