ኦፌኮ የታንዛኒያው የሰላም ውይይት እንዲቀጥል ጥሪ አቀረበ

Your browser doesn’t support HTML5

የኢትዮጵያ መንግሥት እና የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት፣ በታንዛኒያ የጀመሩትን የሰላም ድርድር በአፋጣኝ እንዲቀጥሉ ተቃዋሚው የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ(ኦፌኮ) ጥሪ አቅርቧል።

ፓርቲው በትላንትናው ዕለት በሰጠው መግለጫ ላይ የተናገሩት የፓርቲው ሊቀ መንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና፣ የሰላም ድርድሩ እንዲሳካ ፣ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እና የሚመለከታቸው አካላት እገዛ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

በሌላም በኩል፣ የአገራቸው የነፃነት ቀን በተከበረበት ሥነ ሥርዓት ላይ የተናገሩት፣ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ጉዳይ ፈጻሚ አምባሳደር ትሬሲ ጃኮብሰን፣ በመንግሥት እና በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት መካከል ቀጣይ ውይይቶች እንደሚኖሩ ተስፋ እናደርጋለን፤ ብለዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡