የአማራ ክልል ልዩ ኃይሎች ከትግራይ ለቀው ወጡ

Your browser doesn’t support HTML5

ከኢትዮጵያ ጦር ጎን ተሰልፈው ከትግራይ ተዋጊዎች ጋር ሲዋጉ የነበሩት የአማራ ክልል ልይ ኃይሎች በኅዳር ወር በተደረሰው የሰላም ስምምነት መሰረት ከሽሬ እና አካባቢው ለቀው መውጣታቸውን የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አስታወቀ።

መከላከያ ሰራዊቱ ዛሬ ሐሙስ ባወጣው መግለጫ የአማራ ክልል ኃይሎች ከተባሉት አካባቢዎች ለቀው እንዲወጡ መታዘዛቸውን ያስታወቀ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል አበባው ታደሰ የክልሉ ኃይል ሲወጣ መመልከታቸውን ተናግረዋል።
በአክሱምና ሽሬ መካከል በምትገኘው ሰለኽለኻ በተባለች አካባቢ እንደሚኖሩ በስልክ የነገሩን አንድ ስማቸው እንዲጠቅ ያልፈለጉ የአካባቢው ነዋሪ ከአራት ቀናት በፊት ቁጥራቸው የበዛ አውቶብሶች የታጠቁ ኃይሎች ይዘው ከከተማው ሲወጡ መመልከታቸውን ገልፀውልናል።

ሆኖም ከትግራይ ባለስልጣናት እስካሁን የተሰጠ አስተያየት የለም።