ብርቱካን ሚደቅሳ መልቀቂያ አስገቡ

Your browser doesn’t support HTML5

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ሥራ መልቀቂያ ጥያቄ ለመንግሥት ማስገባታቸውን አስታወቁ።

ኃላፊነታቸውን ለመልቀቅ የወሰኑት በጤና ችግር ምክንያት እንደሆነ ብርቱካን ገልፀዋል።

የቦርዱን ተዓማኒነት በማሻሻልና የፖለቲካ ፓርቲዎችን እንቅስቃሴ በመደገፍ በኩል የተሣካ ሥራ አከናውኛለሁ ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል።

ከመንግሥት በኩል የተሰጠ ምላሽ እስካሁን አልተሰማም።