በሶማሊያዎቹ ሁለት የአጥፍቶ ጠፊ ቦምብ ፍንዳታ 15 ሰው ተገደለ

Your browser doesn’t support HTML5

የሶማሊያ ባለሥልጣና ትናንት ረቡዕ በማዕከላዊ ኺራን ክፍለ ግዛት በደረሱ ሁለት የቦንብ ፍንዳታዎች በትንሹ 15 ሰው መሞቱን አስታውቀዋል።

ጥንዶቹ የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃቶች የደረሱት ማኻስ በተባለቸው ከተማ ትናንት ረቡዕ ማለዳው ላይ ነው። በኺራን ክፍለ ግዛት ውስጥ ያለችው መኻስ ከተማ የምትገኘው ከሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃድሾ በስተስሜን 300 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ ነው።

በመንግሥት ቴሌዥን ስለጥቃቱ መግለጫ የሰጡት የከተማይቱ ከንቲባ ሙኒ መሀመድ ሃለኔ ተሸከርካሪ ላይ የተጠመዱት ሁለቱ የቦምብ ጥቃቶች በመኖሪያ ቤታቸው ላይ እና በፌዴራሉ መንግሥት፣ የምክር ቤት አባል መኖሪያ ቤት ላይ የተነጣጠሩ መሆኑን ተናግረዋል።

በጥቃቱም በርካታ ጉዳቶች መድረሳቸውን ገልጸዋል፡፡