ሱዳናውያን ስደተኞች በሺሕዎች ወደ ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ እየጎረፉ ናቸው

Your browser doesn’t support HTML5

በአገራቸው የሚካሔደውን ጦርነት ሸሽተው የተሰደዱ፣ ቁጥራቸው ከ13ሺሕ በላይ የሚኾኑ ሱዳናውያን፣ በመካከለኛዋ የአፍሪካ ሪፐብሊክ ውስጥ ከምትገኘው የአም ዳፎክ መንደር ደርሰዋል።

ገና ከስደት ከደረሱት ውስጥ አብዛኞቹ፣ ከደቡብ ዳርፉር የኒያላ ከተማ የመጡ ሴቶች እና ሕፃናት ይገኙባቸዋል። እንደ ስደተኞቹ ገለጻ፣ ወደ አም-ዳፎክ በሚወስደው መንገድ በጉዞ ላይ ሳሉ፣ በታጣቂዎች፥ ማስፈራራት፣ ዘረፋ፣ ድብደባ እና ጾታዊ ጥቃቶች የደረሱባቸው በርካታ ሰዎች መኖራቸው ተጠቁሟል።

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።