በተመድ የሱዳን አምባሳደር “የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ወንጀል ቀጥሏል” ሲሉ አስጠነቀቁ

Your browser doesn’t support HTML5

“በፈጥኖ ደራሽ ልዩ ኃይሉ የሚደገፉ ታጣቂዎች፣ ወንጀል መፈጸማቸውን ቀጥለዋል፤” ሲሉ፣ በተመድ የሱዳን ቋሚ መልዕክተኛ አስጠነቀቁ። በመንግሥታቱ ድርጅት የሱዳን ሪፐብሊክ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር አል ሀሪዝ ኢድሪስ አል ሀሪዝ፣ ትላንት ኀሙስ፣ ለጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር፣ “የሱዳንን መንግሥት ለመገልበጥ የተነሡ ታጣቂዎች፣ ወንጀል መፈጸማቸውን ቀጥለዋል፤”ብለዋል።