ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በቅርቡ ሞስኮን እና ኪቭን ሳይጎበኙ እንደማይቀሩ ገለጹ

Your browser doesn’t support HTML5

የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በቅርቡ ወደሩስያ እና ወደዩክሬን ለመጓዝ ተስፋ እንደሚያደርጉ ገለጹ።

የቫቲካን የውጭጉዳይ ሚኒስትር ፒየትሮ ፓሮሊን የሞስኮ ጉብኝታቸውን በሚመለከት ከሩስያ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ጋር እየተነጋገሩ መሆናቸውን ርዕሰሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ለሮይተርስ በሰጡት ቃል አመልክተዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ወደሞስኮ እና ኪየቭ ለመጓዝ የሚያስቡት በቅርቡ በካናዳ ከሚያካሂዱት ጉብኝት በኋላ ሲሆን ሞስኮን ለመጎብኘት ከበርካታ ወራት በፊት ጠይቀው እንደነበር እና በጊዜው ከሩስያ መንግሥት በኩል " ጊዜው አሁን አይደለም " የሚል መልስ ተሰጥቷቸው እንደነበር ጠቅሰው አሁን ግን ያ አቋም ሳይቀየር እንዳልቀረ ፍንጭ ሰጥተዋል።