ተስፋ ሰጭ ቃላት የተላበሰው የቀዳማዊት እመቤት ጂል ባይደን የአፍሪካ ጉብኝት

Your browser doesn’t support HTML5

የዩናይትድ ስቴትስ ቀዳማዊት እመቤት ጂል ባይደን በናሚቢያ እና በኬኒያ ያደረጉትን ጉብኝት ባለፈው እሁድ አጠናቅቀዋል፡፡ በቀዳማዊት እመቤትነታቸው አፍሪካን ሲጎበኙ ይህ የመጀመሪያ ጊዜያቸው ነው፡፡

በመሠረቱ ጂል ባይደን የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ባለስልጣን አይደሉም፡፡ ቢሆንም ተወዳጅነታቸው፡ በመምህርነት ያካበቱትን ተሞክሮ ብሎም የእናትነት ተምሳሌትነታቸው በቆይታቸው ባደረጓቸው ንግግሮች ተንጸባርቋል፡፡

ጉብኝታቸውን የረሃብ እና የዕኩልነት መዛባት ጉዳይ ትኩረት እንዲያገኝ መልእክት ለማስተላለፍ ብቻ ሳይሆን “ዓለምን ማን ይምራት ?” የሚለውን ጠለቅ ያለውን ጥያቄም ለማንሳት ተጠቅመውበታል፡፡ የአሜሪካ ድምጿ አኒታ ፓወል ከናይሮቢ ኬኒያ ያጠናቀረችው ዘገባ በሴቶች እና ቤተሰብ ፕሮግራም ይቀርባል፡፡