ኃይለማርያም ደሣለኝ ቻይና ሄዱ

  • ሰሎሞን ክፍሌ

አምባሣደር ዲና ሙፍቲ፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ - ፎቶ - ከፋይል የተገኘፎቶ - ከፋይል የተገኘ




Your browser doesn’t support HTML5

ኃይለማርያም ደሣለኝ ቻይና ሄዱ


የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ ከሕዝባዊ ቻይና ሪፑብሊክ ፕሬዘዳንት በቀረበላቸው ግብዣ መሠረት የሦስት ቀናት ይፋ ጉብኝት ለማድረግ ወደ ቤይጂንግ በርረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያምና በርሣቸው የሚመራው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በዚህ ጉብኝቱ ወቅት ከፕሬዘዳንቱ፣ ከብሔራዊ ኮንግሬሱ ሊቀመንበርና ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በሁለቱ ሀገሮች፣ በአፍሪቃና ዓለምአቀፍ ጉዳዮች ላይ ይነጋገራሉ ተብሏል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩን የቻይና ጉብኝት አስመልክቶ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሣደር ዲና ሙፍቲ ለቪኦኤ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

አምባሣደር ዲና ሙፍቲ ከሰሎሞን ክፍሌ ጋር ያደረጉትን ቃለምልልስ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡