በጉራጌ ዞን የም/ቤት አባላትን ጨምሮ ብዙ ሰው መታሰሩን ነዋሪዎች ገለፁ

Your browser doesn’t support HTML5

በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን ያለመከሰስ መብታቸው ያልተነሳ የምክር ቤት አባላትን ጨምሮ ብዝ ሰው መታሰሩን ነዋሪዎችና አንድ የሕግ ባለሞያ ገለፁ። እስሩ ክልል ከመሆን ጥያቄ ጋር ሊያያዝ ይችላል የሚል ጥርጣሬ እንዳላቸውም ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲም አምስት አባላቱ እንደታሰሩበት አስታውቋል።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን 40 ሰው መታሰሩን አረጋግጦ የታሰሩበት ምክኒያት ግን “ብጥብጥ በማስነሳትና በሕገ ወጥ ድርጊት ስለተጠረጠሩ ነው” ብለዋል።

[ሙሉውን ዝግጅት ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ]