የአንጋፋው ኤርትራዊ አርቲስት ግርማይ ሰሎሞን ግለ ታሪክ

Your browser doesn’t support HTML5

አብዛኛውን ጊዜውን ከአንጋፋ ኢትዮጵያውያን አርቲስቶች ጋራ ያሳለፈው የአንጋፋው ኤርትራዊ አርቲስት ግርማይ ሰሎሞን የሕይወት ታሪክ እና ሥራዎች ላይ የሚያጠነጥን መጽሐፍ ለንባብ በቅቷል።

በመጽሐፉ፣ ከአርቲስቱ ሕይወትና ሥራ በተጨማሪ የኤርትራ ዘመናዊ ሙዚቃ ታሪክ፣ እንዲካተት መደረጉን የመጽሐፉ አዘጋጅ ዘመንፈስ ሃይለ ገልጿ።

ከአሜሪካ ድምፅ ጋራ ቆይታ ያደረገው፣ የመጽሐፉ ጸሐፊ ዘመንፈስ ሃይለ፣ መጽሐፉ፥ በነፍስ ኄር አርቲስት ግርማይ ሰሎሞን ዜና ሕይወት እና ሥራዎች፣ እንዲሁም የኤርትራን ዘመናዊ ሙዚቃ ኣመሠራረት እና ተያያዥ ጉዳዮች ያካተተ እንደሆነ ገልጿል፡፡