አማራ ባንክ ነገ አገልግሎቱን በይፋ ይጀምራል

Your browser doesn’t support HTML5

አማራ ባንክ፣ ከፊታችን ቅዳሜ ሰኔ 11 ቀን አንሥቶ ሥራውን በይፋ እንደሚጀምር፣ የባንኩ ሓላፊዎች ትላንት በሰጡት ጋዜጣዊ መገለጫ አስታውቀዋል፡፡

የባንኩ የማርኬቲንግ እና ብራንዲግ ዳይሬክተር አቶ አስቻለው ታምሩ፣ ባንኩ በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ፥ 6.5 ቢሊዮን ብር ካፒታል በማስመዘገብ፣ ከ160ሺሕ በላይ የአክስዮን ባለድርሻዎችን በማሳተፍ እና ከ70 በላይ ቅርንጫፎችን በመክፈት የፋይናንስ ግብይቱን የሚወጥን ባንክ እንደኾነ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡

ስለ ባንኩ አመሠራረት አቶ አስቻለውን ጨምሮ የምጣኔ ሀብት ባለሞያዎችን ከዋሽንግተን፣ ከደብረ ብርሃንና ከወልዲያ ዩኒቨርስቲዎች ያነጋገረው ደረጀ ደስታ ተከታዩን አዘጋጅቷል፡፡